የኤርትራ መንግስት አሰልጥኖ የላካቸው የሽብር ተላላኪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2008 (ኤፍ.ቢ.ሲ)

6b8e3c4a0789f2671e742b0e3869a481_XL

 

የኤርትራ መንግስት አሰልጥኖ የላካቸው የሽብር ተላላኪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ። የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎትና የፌዴራል ፖሊስ የፀረ ሽብር የጋራ ግብረ ሃይል ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላኩት መግለጫ፥ እነዚህ የሽብር ተላላኪዎች ኤርትራ ውስጥ በሻዕቢያ የሽብር ስልጠና ሲሰጣቸው የቆዩ መሆናቸውን ገልፀዋል። ከመነሻ እስከ መድረሻቸው ድረስም በብሄራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት የክትትል ጥላ ስር የነበሩ ናቸው ተብሏል። የኤርትራ መንግስት ተላላኪዎቹ ስማቸውን በመቀየር የኤርትራ የጉዞ ሰነድ ከተዘጋጀላቸው በኋላ ከአስመራ ተነስተው ወደ ኡጋንዳ በአውሮፕላን ቀጥሎም በተሽከርካሪ ወደ ኬኒያ ተጉዘው በሞያሌ በኩል ድንበር ተሻግረው በደቡብ ክልል ደቡባዊ ጫፍ አካባቢ በሚገኝ ጫካ ውስጥ ያልታወቁ መስሏቸው ራሳቸውን በመደበቅ ቆይተዋል ነው ያለው። በዚያም ለተለያዩ የሽብር ተግባራት ሲዘጋጁ ግብረሃይሉ ባካሄደው ኦፕሬሽን ሚያዚያ 28 ቀን 2008 ዓመተ ምህረት በቁጥጥር ስር ውለዋል። የኤርትራ መንግስት ተላላኪዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት ከያዙት የጦር መሳሪያ እና ቁሳቁስ ጋር ነው።በወቅቱ ለማምለጥ የሞከሩ ጥቂት አሸባሪዎችም ተገድለዋል። የፀረ ሽብር ግብረ ሃይሉ በመግለጫው እንዳመለከተው፥ የኤርትራ መንግስት ተላላኪዎቹ በሃገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል በኩል ወደ ሃገር ውስጥ ለመግባት ያደረጉት ተደጋጋሚ ሙከራ የኢፌድሪ መከላከያ ሰራዊት ሀይል፣ የአማራ እና ትግራይ ክልሎች የፈጥኖ ደራሽ ፖሊስ ሃይሎች በወሰዷቸው ተከታታይ እርምጃዎች ሲከሽፉ ቆይተዋል። ይህ አልሳካ ሲል በደቡብ የሃገሪቱ ክፍል በኩል ያደረጉት ሌላ የቀቢጸ ተስፋ ሙከራ በእንጭጩ መቀጨቱን ነው መግለጫው ያስታወቀው። በቁጥጥር ስር በዋሉት የሻዕቢያ ተላላኪዎች ላይ የተጀመረው ምርመራ ተጠናክሮ መቀጠሉንም የግብረሃይሉ መግለጫ አመልክቷል። ሌሎች ዜናዎች:

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *