
እኛ አንደበታችን ቢታሰር፣ በድንጋጤ ብንደነዝዝ እንኳ፤ ያፈሰሱት ንጹህ ደማቸው ከመሬት ስር ሆኖ ይጮኻል። እነዚህ በአርሲ ምድር በግፍ የታጨዱት ወገኖቻችን፣ የአንድ ወር ታሪክ ሳይሆኑ የዘመን የማይሻር ጠባሳዎች ናቸው።
እንደ ሰው መኖር፣ በሰላም ወጥቶ መግባት ይገባቸው ነበር፤ ዛሬ ግን በሳጥን ታሽገው የፍትህ ያለህ እያሉን ነው። ለጥቂት የፖለቲካ ትርፍ ተብሎ የሰው ነፍስ እንደ ቅጠል ረገፈ። ይህ ግፍ ግን ለሚያስተውል ሕሊና ትልቅ የሰላም ጥሪና የፍትህ ጥያቄ ነው። ከፖለቲካ ስሌት በላይ የሰው ልጅ ክብር ይቅደም!
ፈጣሪ ሆይ… ካንተ በቀር ማን አለን? አንተ ፍረድ! አንተ እረኛ ለሌላቸው እረኛ ሁናቸው!